Skip to main content Scroll Top

ጽዳት

የጽዳት ሳምንት ሁላችንም እንደምናውቀው ትናትና ማታ ሁላችንም የምግብ እቃዎቻችን አጥበናል የምግብ ማስቀመጫ ማቀዝቀዣችንም አጽድተናል ግን ስንቶቻችን ራሳችን እንደተመለክትን ማውቅ አልተቻልም ይኽ ሳምንት የይቅርታ ሳምንት ይሁንልን:: ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ። ሉቃ 6፡37

በነገው ዕለት ይህን ጥያቄ ይጠይቁ በእግዚአብሔር እኔ ይቅር ተብያለሁ ወይ? የምን ጠይቀው ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ከፈለግን አኛ መጀመሪያ የተጠየቅነዉን መመለሰ ይገባል ::

እነዚህ የጌታ ትምህርቶች ይህን እናድርግ ዘንድይረዱናል::
ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። ማቴ 6፡14-15
አንተ ይቅር ተብለሕ ከሆነና ያንን ካመንክ ይቅር ማለት አልብህ ያን ካላደረክ ግን የተሰጠህ ይቅርታ ካንተ ይወሰዳል::
መቈጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። የሚከፍለውም ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ። ስለዚህ ባሪያው ወድቆ ሰገደለትና። ጌታ ሆይ፥ ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው። የዚያም ባሪያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፥ ዕዳውንም ተወለት። ነገር ግን ያ ባሪያ ወጥቶ ከባልንጀሮቹ ከባሮቹ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና። ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው። ስለዚህ ባልንጀራው ባሪያ ወድቆ። ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ ብሎ ለመነው። እርሱም አልወደደም፥ ግን ሄዶ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወኅኒ አኖረው። ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሮችም ያደረገውን አይተው እጅግ አዘኑ፥ መጥተውም የሆነውን ሁሉ ለጌታቸው ገለጡ።32 ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ። አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው። ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው። ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል። ማቴ 18፡26-37

አገልጋዩ የተናገረው እዳውን መክፈል እንደማይችል ነው ያቀረበው ጥያቄም ይቅርታ አንዲደረግለት ነው:: በዙ እዳው ተሰዝሮለት ግን እርሱ ተበድሮ ያበደረውን ይቅር ማለት አቃተው ። አሁን ጥያቄው ይቅር መባልህን አውቀሐል ወይ ነው:: እሱን ካለወክ ቆም ብለሕ አስብ ሰው በስጋው ይቅር ባይ አይደለም ሰው በቀልኛ ነው ከምህርት አምላክ ምህረትን መቀበል አለበት አሁንም ምህረትን ለመቀበል ፈቃደኛ ሁን::
ሁለተኛ ቀን
እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ።ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት። እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። ማርቆ 11፡23-26
እየነገረህ ያለው ተራራ የሚያፈርስ እምነት ሊኖርህ ይችላል ግን ይቅር ካላልክ ፈይዳ የለውም ሃያ አራት ሰዓት ቁምኽ ብትጸልይ የምላስ ጅምናስቲክ ካልሠራሕ በቀር እግዚአበሔር አያየውም:: ጠላትን የምታሸንፈው እርሱ በሔድበት መንገድ ሒደሕ አይደለም ሌላ ዘዴ ተጠቀም:: ይህን ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ሲል ይመክርሐል::
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ። ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ። ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ። ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና። ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና። ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ። ሮሜ 12፡16-19
ይህ ነው ጠላቴ የምትለው ክፍል ያለሔደበት መንገድ በዚህ ሔደሕ አሽንፈው ግን ማሸነፍ ብቻ አይደለም የእሳት ክምር ትከምርበታለህ ከዚህ ጋር የይቅርታ ሰዎች ካለሆን በዕሥር ቤት ውስጥ መሆናች ግን መዘንጋት የለብንም::
ክፉን ልብ የምያለዝበዉ ሸካራ አንደበትን የሚያለሰልሰው ይቅርታ ነው:: አንድ ተቀየምኩ ያለ ሰው ምላሱን አሾሎ ሊሰድብህ ሲመጣ ይቅርታ ብትለው ምን የሚል ይመስለሓል:: አሁን ይህን ይመስላል ልልህ አልችልም ሞክረሕ ብትምለከትው ግን የበለጠ ፈውስ ታገኛለህ::

ሦስተኛ ቀን
ይቅር የምትለው ዘም ብለህ አይደለም አንተ ራስህ ይቅር ስለተባልክ ነው ::
በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም። ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ። እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ:: እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ። በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ። ቆላስይስ 2፡13
አራተኛው ቀን
አንተ ይቅር የተባልኽው ተወዳጅ በነበርክበት ጊዜ ወይም የሚወደድ ባህርይ ሰላለህ አይደለም:: ግን ጋና ሃጤአተኛ ሁነህ ሳለ ይቅር ተባልክ ይህን ስታስብ ነው የይቅርታ ጉልበት የመታገኘው::
እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ። እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ። ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ። በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት።
አምስተኛው ቀን
የራሰዎ የሥራ ቀን ነው:: አራት ቀን ያነበቡትን ዙረው ይመልክቱት:: ቀጥለው አስቀይመውኛል ያሏቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ይያዙ:: ይቅር ማለት ካቃትዎ በእግዚአብሔር ፊት ይዘው ይቅርቡ:: ጥያቄዎ እንዲህ ቢሆን እግዚአብሔር ሆይ አንተ እኔን ይቅር ማለትህን ይህን ሰው ወይም ይህችን ሰው ይቅር እንድላት ወይም እንድለው ኅይል ሰጠኝ ብለው ይጽልዩ:: በሌላ አባባል የእግዚአብሔርን ይቅርታ ይለማመዱ ማለት ነው::

Leave a comment