Skip to main content Scroll Top

ታላቁ ጾም

PostFeaturedImage_KibreQidusan_Final (3)

የቃሉ ፍች፦ ሥርወ ቃሉ ግእዝ ነው፤ ጾመ ተወ ተከለከለ ታረመ ማለት ነው። በሥርዐተ ጾም ደግሞ ጾም ማለት ለተወሰነ ሰዓት ከእሕል ከእውሀ መከልከል፤ ለተወሰኑ ሳምንታት ወይም አውራሕ ወይም እለታት ደግሞ ሥጋን አካልን ከሚገነቡና የሥጋን ፍትዎትን ከሚያጠናክሩ ከፍተኛ ኃይልና ፕሮቲን ካላቸው መባልዕት መከልከል፤ የሥጋን ፍላጎት ማድከም፤ ደመነፍስ ለነባባቢት ነፍስ ሥጋዊ ሕይዎት ለመንፈሳዊ ሕይዎት እንዲታዘዝ ማድረግ ማለት ነው።
ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 15«ጾምሰ ተከልኦተ ብእሲ እመ መብልእ በጊዜ እውቅ— ፈቂዶ ኪያሁ ከመያድክም ኃይለ ፍትወት ወትትአዘዝ ለነፍስ ነባቢት።» ይላል። ይህም« ጾም የሰው ለታወቀ ጊዜ ከምግብ መከልከል ነው—የሥጋ ፍላጎቱን ያደክም ዘንድ ለነባባት ነፍስም ትገዛ ዘንድ» ማለት ነው።

ጾም ከሥርዐተ አምልኮ አንጻር ሲታይ ከጸሎት፣ ከስግደትና ከምጽዋት ጋር አብሮ የሚሄድ መንፈሳዊ አገልግሎት ማለት ነው። ሰው በጾምና በጸሎት በሥጋው ለእግዚአብሔር ይገዛል፣ ፈጣሪውንም ያመልካል። ሰው በምጽዋት ደግሞ በገንዘቡ ፈጣሪውን እግዚአብሔርን ያመልካል። በገንዘቡም ለእግዚአብሔር ይገዛል። በጸሎትም ሰው በመንፈሱና በአእምሮው ለእግዚአብሔር ይገዛል። በመሆኑም የሰውልጅ በሥጋው በነፍሱና በአእምሮው ፈጣሪውን ያመልክ ዘንድ መጾም ነስገድ መመጽዎት አለበት። ጾም ጸሎት ስግደትና ምጽዋት በአንድላይ የሚሰበኩት ለዚህ ነው።
የጾም ክፍሎች ሁለት ናቸው፤ የግልና የመኅበር በመባል ይታወቃሉ።
የግል ጾም፦ ሰው በግሉ የሚጾመው በገዛ ፈቃዱ ከእግዚአብሔር ምልክት ፈላጎ ወይንም እራሱን ለመቅጣት እራሱን ለመመርመር በስውር ማንም ሳያውቅ የሚጾመው ነው። በቀኖና መልክ የሚጾመው የንስሐ ጾምም ቁጥሩ ከግል ጾም ነው። የግል ጾም በስውርና ማንም ሳያውቅ ይጾማል /2 ሳሙ 12፥22፣ ዘዳ 9፥9-19/።
የማኅበር ጾም፦ በብሉይ ኪዳን ጾም እንደዛሬው ሁሉ ይታወጅ ነበር። ሕዝበ እግዚአብሔር በዓመት ውስጥ የሚጾም የአዋጅ ጾም ነበራቸው። እንዲሁም አገርን አንድነትን የሚጎዳ ችግር ሲያጋጥም ወይንም ሕዝቡ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢዓት ሰርቶ አማላክ በነቢያት በኩል ሲወቅሰው በንድነት በማኅበር ይጾሙ ይጸልዩ ያለቅሱና በልማናቸውም ምህረትን ያገኙ ነበር/ መሣ 20፥26፣ኢዩ 1፥14፣ዘሌ 16፥29-31፣ ዘካ 8፥19፣ አስቴ 9፥31/።
ከዚህ የተነሳ በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትም የተወቁ በዓመት የሚጾሙ ሕዝቡ ሁሉ እንዲጾማቸው የታዘዘዙ ሰባት የጾም ጊዜያት አሉ። እነሱም
1 ዐቢይ ጾም
2 ጾመ ድኅነት ማለትም ዐርብና ረቡዕ
3 ጾመ ሐዋርያት
4 ጾመ ፍልሰታ
5 ጾመ ነቢያት
6 የጥምቀት ዋዜማ የጋድ ወይም የለውጥ ጾም
7 ጾመ ነነዌ ናቸው።
የጾም መንፈሳዊ ትርጉም፦ ጾም ማለት ከሥጋ ከቅቤ ከወተት መከልከል ብቻ አይደለም። እውነተኛው ጾም የሕይዎት ለውጥ ነው። ቅዱስ ያዕቆብ«አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው» ይላል / ያዕቆ 1፥26/።
ቅዱስ ያሬድም በጾመ ድጓው «ይጹም ዐይን ይጹም ልሳን እዝንኒ ይጹም እምሰሚዓ ሕሱም በተፋቅሮ» « በፍቅር ዐይን ይጹም፣ አንደበትም ይጹም፣ ጀሮም ክፉ ከመስማት ይጹም።» ብሎ መንፈሳዊ ጾም ምንመምሰል እንዳለበት አስተምሯል።
ጾም የረሐብ አዋጅ አይደለም የሕይዎት መስተካከል የልብ መሰበር ምህረትን እና ጽድቅን የመራብ የመፈለግም ሕይወት ነው።
ጾም መራብና መጸማት ሳይሆን የምላኮ መንገድ ነው።
ጾም አጥቶ መቼግር ሳይሆን መተው ነው።
ጾም ሰውነት ጬመረ ሰውነትሽ ጨመረ ሲባል መፍረቅ የጮኸበት ያክል በመደንገጥ ምግብ ቀንሰው ወይምግብ ዐይነት መርጠው እንደ ሚመገቡ ሰዎች ሰዎች የአካለ ሥጋ መእተካከያ አመጋገብ ስልት ሳይሆን የሕይዎት ለውጥና መንፈሳዊ ልምምድ ነው።
ጾም በሕይዎታቸው ተስፋ ቆርጠውና ተናደው ጦማቸውን እንደሚያድሩ ሰዎች የረሀብና የብስጭት የተስፋ መቁረጥም ሕይዎት ሳይሆን የቅድስና የበረከት ራስን የመግዛት ሕይዎት ነው። አንድ አንድ ሰዎች ጾም አይታዎጅም ይላሉ። በሆዳሙ ዓለም ላይ ሊታዎጅ የሚገባው እውነተኛ አዋጅ ጾም ነው። ልብላና ልጠጣ ነገ እሞታለሁ ለሚለው ዓለም የጾም አዋጅ ያስፈልገዋል።
ለቤተ ክርስቲያን ዐለምን ለጾምና ለጸሎት ከማዘጋጀት በንስሐ በጾም በጸሎት ወደ እግዚአብሔር እንድትመለስ ከማስተማር የበለጠ ነገር የላትም።
ጾም የመንፈሳዊ ሕይዎት ተጋድሎ ሁሉ የመጀመሪያ ኃይል ናት። ስለ ዚህም በጾም የተጠቀመ አንድ ቅዱስ አባት በጽሐፈ መነኮሳት« እስመ ጾም እማ ለጸሎት ወእኅታ ለአርምሞ ወነቅዓ ለአንብእ ወጥንተ ኩሉ ገድል ሠናይ፤ ጾም የጸሎት እናት የዝምታ ምንጭ እንባ ምንጭ የመልካም ተገድሎ ሁሉ መሰረት ናት።» ይላል።
ጾማችን ወደተሻለ መንፈሳዊ ሕይዎትና ተጋድሎ የማያሸጋግር፣ በጎ አድራጎትና ትሕትና ፍቅርና መተሳሰብ የጎደለው ከሆነ ዋጋ የለውም። እግዚአብሔር በነቢዩ በኢሳያያስ «እኔ የመረጥሁት ጾም የበደልን እሥራት ትፈቱ ዘንድ፣ የከበደውን ቀንበር ትሽሩ ዘንድ፣ የታሰሩትን ዓርነት ትለቁ ዘንድ ቀንበሩን ሁሉ ትፈርሱ ዘንድ አይደለምን?» ብሏል/ኢሳ 58፥3-7/።
የጾም ጥቅም ፦
1 ከመብል ከመጠጥ የተነሳ የሰው ልቡና እንዳይደነዝዝና አእምሮውም እንዳይፈዝና አእምሮውም እንዳይደነዝዝ አጥንቶ ብቃት ተለይቶ እንስሳ መስሎ ሥጋውን ሲያከብር ፈጣሪውን ሳያውቅና ሳያከብር በድንገት ሞት ሐዘን መከራ እንዳይደርስበት መዳኃኒታችን መድኃኒታችን አስጠንቅቋል። « ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካርም — እንዳይከብድ ያም ቀን በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።»/ ሉቃ 21፥34/። ብዙ መብል መንፈሳዊ ሕይዎትን ብቻ ሳይሆን የሥጋዊ ሰውነትን ጤና ሳይቀር ያቃውሳል። ማንኛውንም የሥጋ ፈቃድ ያስለውጣል፤ኃላፊነትን እንዲዘነጉ ያደርጋል፤ ጾም ግን የነፍስም የሥጋም መድኃኒት ነው። ለሰውነት ንጽሕናንና ጤንነትን፣ ኃላፊነት እንዲሰማንና በትጋት እንድንሰራ ያነቃቃናል።
2 መብል መጠጥ ያገዝፋል፣ ልብን ያደነድናል፣ከረቂቅ አምላክ ያርቃል፤ ጾም ሥጋን ይቀድሳል፤ መንፈስን ያነቃቃል፤ ነፍስ በጾም ትጎለምሳለች ሰውም ለፈጣሪ ማደሪያ ይሆንል።
3 ስንጾም ይርበናል ስለዚህ ምግብ ያምረናል፤ በዚህ ጊዜ የወንድሞቻችንና እህቶቻችንን እረሐብ እናስባለን። የተራቡትን እንድንመግብ ያነሳሳናል። እኛም በተፈጥሮአችንን የእግዚአብሔርን መግቦት እናስባለን። እግዚአብሔርንም እናመሰግናለን። እረሀብም በዓለማችን ላይ እንመጣ እጸልያለን። በምንጾምበት ጊዜ ለቁርስ ለመክሰስ የሚሆነውን ለረሀብተኞች እናውለዋለን፤ በጎ ሥራም እንሰራበታለን። ማካፈልን መተዛዘንን እንማርበታለን።
4 በጾም በጸሎት በላያችን የምሰለጥነውን ክፉ መንፈስ ድል እንነሳዋለን። በፍቅረ እግዚአብሔር መነጠቅ የአጋንንትን ሠራዊት ማራቅ የምንችልበት ኃይል እንገኛለን። አብሮ አደጉንም ጠላት በጾም ኃይል ድል እንነሳዋለን/ማቴ 17፥21/።
ስብሐት ለአምላክ አሜን!
መምህር ልዑለቃል አካሉ።
ክብረ ቅዱሳን መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን።
ሲያትል።

Leave a comment